የመንገድ እይታ 15ኛ ዓመትን በማክበር ላይ
የመንገድ እይታ በ2007 የዓለምን የ360-ዲግሪ ካርታ ለመፍጠር የማይታመን በሚመስል ሃሳብ ተጀምሯል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ አንድ ላይ ከ220 ቢሊዮን በላይ ምስሎችን እና ከ10 ሚሊዮን ማይሎች በላይ በመላው 100 አገሮች እና ግዛቶች ቀርጸናል።
በዚያውም እርስዎ ህዋን፣ ውቅያኖስን እና በመካከሉም አስደናቂና አስፈሪ ቦታዎችን አስሰዋል እና ሁልጊዜም ወደቤትዎ የሚሄዱበትን መንገድ አግኝተዋል።
በመንገድ እይታ ላይ ምን አዲስ ነገር አለ?
አሁን ይለቀቃል፦ ወደ ኋላ ወደነበረ ጊዜ ይጓዙ
አሁን የGoogle ካርታዎች መተግበሪያ ላይ በየመንገድ እይታ ታሪካዊ ምስል ቦታዎች በጊዜ ሂደት እንዴት እንደተቀየሩ ማየት ይችላሉ።
የGoogle ካርታዎች መተግበሪያን ያውርዱ።
የእኛ 15 ተወዳጅ እይታዎች
ከሞንጎሊያ የበረዶ ፌስቲቫል እስከ የቲቲካካ ሃይቅ የሚንሳፈፉ ቤቶች፣ ፕላኔታችን ከምታቀርባቸው አንዳንድ በጣም አስደናቂ እይታዎች ይውሰዱ።