የፎቶግራፊ ምንጮች
የመንገድ እይታ ፎቶዎች ከሁለት ምንጮች ይመጣሉ፣ ከGoogle እና ከአስተዋጽዖ አበርካቾቻችን።
የእኛ ይዘት
በGoogle ባለቤትነት የተያዘ ይዘት ለ«የመንገድ እይታ» ወይም ለ«Google ካርታዎች» እውቅና ይሰጣል። በምስላችን ውስጥ ፊቶችን እና የሰሌዳዎች ቁጥርን በራስ-ሰር እናደበዝዛለን።
ከሌሎች አስተዋጽዖ አበርካቾች የተገኘ ይዘት
በተጠቃሚ-የተበረከተ ይዘት ጠቅ/መታ ሊደረግ የሚችል ስም፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመገለጫ ፎቶ ጭምር አብሮ ይከተላል።
Google እንዴት የመንገድ እይታን እንደሚያቀርብልዎት
የመንገድ እይታ ምስልን ለማጋራት፣ የመሃንዲስ ቡድናችን ከመድረክ በስተጀርባ በርትቶ ይሰራል። የመንገድ እይታን ወደ እርስዎ ለማምጣት ቡድኑ የሚሰራው ስራ በጨረፍታ ይህን ይመስላል።
-
ደረጃ 1
ምስል መሰብሰብ
በመጀመሪያ እየተዘዋወርን በመንዳት በመንገድ እይታ የሚታዩትን አካባቢዎች ፎቶግራፍ ማንሳት አለብን። በተቻለ መጠን ምርጥ ምስል የሚገኝበትን ጊዜና ቦታ ለመወሰን የአየር ንብረትን እና የሰው ብዛትን ጨምሮ ለበርካታ ጉዳዮች ትልቅ ትኩረት እንሰጣለን።
-
ደረጃ 2
ምስሎችን ማሰለፍ
እያንዳንዱን ምስል በካርታው ላይ ከትክክለኛ ቦታው ጋር ለማዛመድ፣ ጂፒኤስ፣ ፍጥነት እና አቅጣጫ ከሚለኩ በመኪናው ላይ የተገጠሙ መለኪያዎች የተገኙ ምልክቶችን እናጣምራለን። ይህም የመኪናውን ትክክለኛ መስመር መልሰን እንድንሰራ፣ እንዲሁም ምስሎችን እንዳስፈላጊነቱ እንድናጋድል እና እንደገና እንድናሰልፍ ያስችለናል።
-
ደረጃ 3
ፎቶዎችን ወደ 360 ፎቶዎች መቀየር
በ360 ፎቶዎች መካከል ክፍተቶችን ለማስወገድ፣ ተከታታይ ካሜራዎች መጠነኛ መደራረብ ያላቸውን ምስሎች ይወስዱና ፎቶዎቹን በአንድ ላይ «በመስፋት» አንድ ባለ 360-ዲግሪ ምስል ያደርጓቸዋል። ከዚያም «ጠርዞችን» ለመቀነስ ልዩ የምስል ማቀነባበሪያ ስልተ ቀመሮችን በመጠቀም ወጣገባነት የሌላቸው መሸጋገሪያዎችን እንፈጥራለን።
-
ደረጃ 4
ለእርስዎ ትክክለኛ ምስል በማሳየት ላይ
የመኪናው ሦስት ሌዘሮች ከገጾች ላይ የሚያንፀባርቁበት ፍጥነት አንድ ህንጻ ወይም እቃ በምን ያህል ርቀት ላይ እንዳለ ይነግረናል፣ እናም 3ል ሞዴሎችን ለመስራት ያስችለናል። ወደ አንድ ቦታ አቅራቢያ ሲንቀሳቀሱ፣ የ3ል ሞዴሉ ለዚያ አካባቢ ሊያዩት የሚመረጠውን የተሻለው ፓኖራማ ይለያል።

ወዴት እንደምናመራ
የእርስዎን ተሞክሮ የሚያሻሽል እና በዙሪያዎ ያለውን ዓለም እንዲያውቁ የሚያግዝዎትን ምስሎች ለእርስዎ ለማቅረብ በየመንገድ እይታ መኪና አማካኝነት በብዙ ሀገሮች በኩል እየነዳን እያለፍን ነው። በቀጣይ መኪና የምንነዳበትን ወይም የምንጓዝበትን አገራት ዝርዝር ይመልከቱ።
ክልል | ወረዳ | ሰዓት |
---|---|---|
{[value.region]} | {[value.districts]} | {[value.datestart| date:'MM/yyyy']} - {[value.dateend| date:'MM/yyyy']} |
ከእኛ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ጉዳዮች ምክንያት (የአየር ንብረት፣ የመንገድ መዘጋት፣ ወዘተ)፣ መኪናዎቻችን ላይሰሩ የሚችሉበት ወይም የተወሰነ ለውጥ ሊኖር የሚችልበት እድል ሁልጊዜ ይኖራል። በተጨማሪም ዝርዝሩ አንድን ከተማ በጠቀሰበት ቦታ፣ በመንዳት በሚደረስበት ርቀት የሚገኙ አነስተኛ ከተማዎችንም የሚያካትት ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ ይያዙ።
የት እንደነበርን
በካርታው ላይ ያሉት ሰማያዊ አካባቢዎች የመንገድ እይታ የት እንደሚገኝ ያሳያል። ለበለጠ ዝርዝር፣ አጉልተው ይመልከቱ ወይም ይህን ይዘት በድር ጣቢያዎቻችን ወይም መተግበሪያዎቻችን ያስሱ።
የGoogle የራሱ የመንገድ እይታ ስምሪት
የእኛን የመንገድ እይታ ስምሪት ያስሱ።
-
የመንገድ እይታ መኪና
በ2007 በዩናይትድ ስቴትስ ከጀመርን ጀምሮ ረጅም ርቀት መጥተናል፤ በሁሉም ሰባት አህጉሮች ውስጥ አካባቢዎችን ለማካተት አሁን የእኛን 360 ፎቶዎች አስፋፍተናል።
-
የመንገድ እይታ ተጓዥ
የመንገድ እይታ በዓለም ዙሪያ ተጨማሪ ቦታዎችን እንዲመርጥ ተጓዥ አስችሎታል - ምንም መኪና፣ ትራይክ፣ ትሮሊ ወይም ስኖውሞባይል በማይደርስባቸው ቦታዎች። ይህ ተለባሽ የጀርባ ጥቅል ከላይ የካሜራ ስርዓት የተገጠመለት ሲሆን በቀላሉ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ መቻሉ ጠባብና ወሽመጣማ የሆኑ ቦታዎችን ወይም በእግር ብቻ የሚደረስባቸውን አካባቢዎች ምስሎች ለመሰብሰብ አስችሎናል። ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ያገኘነው ስብስብ የተወሰደው በወጣገባው ዓለታማ የአሪዞና ግራንድ ካንዬን መልክዓ ምድር ነበር።
-
የመንገድ እይታ ትሮሊ
ጥበብ ወዳድ የGoogle ሰራተኞች የመንገድ እይታ ቴክኖሎችን በዓለም ዙሪያ ባሉ ቤተ-መዘክሮች ሊወስዱት ሲፈልጉ፣ በቤተ-መዘክሮች መግቢያ በሮች በቀላሉ መግባት የሚችል እና በቅርጻ ቅርጾች መካከል መንቀሳቀስ የሚችል ስርዓት መገንባት አስፈለገን። ይህች የመጀመሪያዋ የቤት ውስጥ ሙከራ ሁሉንም አስፈላጊ ቁሳቁሶች በአነስተኛ ፍሬም ላይ ያካተተች ነበረች፦ ትሮሊ የሚል ስያሜ የተሰጣትና የካሜራ ስርዓት የተገጠመላት ትንሽ የምትገፋ ጋሪ። በቤተ-መዘክሮች ውስጥ እይታዎችን ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ዋይት ሀውስ እና የስፖርት ስታዲዬሞች የውስጥ ክፍል አይነት የቤት ውስጥ አካባቢዎችን ጭምር ሰብስቧል።
-
የመንገድ እይታ ስኖውሞባይል
የመንገድ እይታ ካሜራዎችን ብንወስዳቸው አስደሳች ይሆናል ብለን ያሰብነው ሌላው ቦታ ተዳፋቶች ናቸው። በተወሰኑ እሁድና ቅዳሜዎች 2x4ዎች፣ ባለቱቦ ቴፕ እና የማቀዝቀዙን ሁኔታ ለመቋቋም በስኪ ጃኬት የተጠቀለለ ተጨማሪ ደረቅ አንጻፊ በመጠቀም፣ ቡድኑ የመንገድ እይታ መሳሪያውን በስኖውሞባይል ላይ በተሳካ ሁኔታ ማስቀመጥ ችሎ ነበር። የበረዶ ሸርተቴ፣ ስኖውቦርድ እና ስኖውሹ ተጫዋቾች አሁን ዊስለር ብላክኮምብ ተራራን እና ኮረብታማውን፣ በዙሪያው ባሉ ሪዞርቶች የተጋራ በበረዶ-የተሸፈነ መልከዓ ምድርን ማሰስ ይችላሉ።
-
የመንገድ እይታ ባለ ሶስት-ጎማ
ትናንሽ መንገዶች ላሏቸው ከተሞች የመንገድ እይታ ተጓዡን ለመያዝ ጠንካራ የሆነ ተሽከርካሪ ማሰብ ነበረብን። አንዳንድ የተወሰኑ ጠባብ የግንብ መሃል መተላለፊያዎችን ለመድረስ፣ ቡድናችን በኢንዶኔዥያ ውስጥ ያለ ሞተርሳይክል ሴሊስ ሮቢንን ትልቅ መፍትሔ ሆኖ አግኝቶታል። የመንገድ እይታ ባለ ሶስት-ጎማን ይተዋወቁ። ለመንገድ እይታ ተጓዡ ተጨማሪ መረጋጋትን ለመስጠት በተለይ ለዚህ ተሽከርካሪ ተጨማሪ ምሰሶ ተገንብቷል።