በየመንገድ እይታ ታሪኮች ይነሳሱ
ዛንዚባር
የመንገድ እይታ የታመኑ ፎቶግራፍ አንሺዎች ስብስብ፣ «የዓለም ጉዞ በ360 (WT360)» ዛንዚባርን ካርታ ላይ ለማስቀመጥ ከታንዛኒያ መንግስት ጋር ስለሚሰሩት የጋራ አዲስ እቅዳቸው ፕሮጀክት ዛንዚባር ሲያወሩ ይመልከቱ። ፌደሪኮ ዴቤቶ፣ ኒኮላይ ኦሜልቼንኮ እና ክሪስ ዱ ፕሌሲስ የደሴቶችን ካርታ ለመስራት መሰረት ለመጣል፣ የመንገድ እይታ ፎቶግራፊ ላይ የአካባቢውን ሰዎች ለማስተማር እና ማህበረሰቡ ፕሮጀክቱን በራሱ እንዲቀጥል ዘላቂ ሞዴልን ለመገንባት ወደ ታንዛኒያ ተጉዘዋል።
ሚያንማር
የፎቶግራፍ አንሺውን ኒዪ ሊን ሴክ እና ባልደረቦቹን ከ3XVIVR ፕሮዳክሽኖች የተሰራ ድንቅ ስራን በሚያሳየው በዚህ ቪዲዮ ሚያንማርን ያስሱ። 3XVIVR ሚያንማርን በየመንገድ እይታ በኩል ዲጂታል ለማድረግ እና የአገሩን ባህላዊ ቅርስ በ360 ጠብቆ ለማቆየት በማለም ልዩ ለሆነው ፕሮጀክታቸው ብዙ ጊዜን እና ጥረትን መስዋዕት አድርገዋል።
ዚምባብዌ
ታዋንዳ ካንሄማ የዚምባብዌን የመንገድ እይታ ካርታ እንዴት እንደሰራላት ታሪኩን ሲናገር ይመልከቱ። ታዋንዳ ወደ አገሩ ዚምባብዌ የተመለሰው ዋና ከተማ እና የቪክቶሪያ ፏፏቴ መገኛ የሆነችውን ዓለም አቀፋዊ የቱሪስት መዳረሻዋን የሃራሬን የመንገድ እይታ ምስል በGoogle ካርታዎች ላይ የማስቀመጥ ግብ ይዞ ነበር። በቅርብ ጊዜም በዚምባብዌ ዙሪያ ያሉ ሌሎች ቁልፍ አካባቢዎችን ለማካተትም ፕሮጀክቱን አስፋፍቷል።
ኬንያ
አንዳንድ የአካባቢ አስጎብኚዎችን እና የመንገድ እይታ የታመኑ ፎቶግራፍ አንሺዎች የኬንያን ካርታ ሲሰሩ ይተዋወቁ። ዓለም የኬንያን በጣም ልዩ የሆነ ውበት ተሞኮሮ እንዲኖረው የማገዝ ምኞታቸው ይህንን ግብ ለማሳካት እንደ ዋነኛ መሣሪያ ለመጠቀም ወደ የመንገድ እይታ በቀጥታ መርቷቸዋል።
አርሜኒያ
ከጆ ሃኮቢያን፣ ለትልፍ ያልሆነ ድርጅት Armenia360 መስራቾች ውስጥ አንዱ ከሆነው ይስሙ። ጆ የቅድመ አያቶቹ ጥንታዊ መሬትን ካርታ ለመስራት የሄዱበትን የቡድኑን ጉዞ በተመለከት ለንደን ላይ በተካሄደው የ2019 የመንገድ እይታ ጉባዔ ላይ ተናግሯል። ይህ በየመንገድ እይታ ካርታ ላይ ለእሱ አስፈላጊ ያሆኑትን ቦታዎች ለማስቀመጥ ማንኛውም ሰው እንዴት መብቃት እንደሚቻል የሚነግር ታሪክ ነው።
ቤርሙዳ
የቤርሙዳ የቱሪዝም ባለሥልጣን፣ የመዳረሻ የማሻሻጫ ድርጅት የሆነ፣ የመንገድ እይታ ምስልን ለመሰብሰብ የማይልስ ሽርክና የመንገድ እይታ የታመነ ወኪልን እንዴት እንደቀጠረ ይወቁ። የማይልስ ሽርክና የቤርሙዳ የቱሪዝም ባለስልጣንን በGoogle ካርታዎች ላይ የመስመር ላይ ተገኝነታቸውን ለማትባት እና አካባቢያዊ የንግድ ግኝትን ለማጎልበት፣ በተጨማሪም ቱሪስቶች ጉዞን እንዳቀዱት (ወይም በቀን በሚያልሙት!) ቤርሙዳን በምናባዊ እንዲያሰሱ በማገዝ ደግፏል።
ቶንጋ
የግሪድ ፓስፊክ መስራቾች፣ ታኒያ ዎልፍግራም እና ዊኩኪ ኪንጊ ቶንጋ ላይ የነበራቸውን የካርታ ስራ ጉዟቸውን ሰንደዋል። የቶንጋን እና ሌሎች የፓስፊክ ደሴቶችን ባህል ለማስተዋወቅ የመላውን ደሴቶች ካርታ ለመስራት እና ወደ የመንገድ እይታ ለማከል ትልቅ እቅድ አስጀምረዋል። አስገራሚ ታሪካቸውን እዚህ ይመልከቱ።